ከማዕድን ላኪዎችና የከበሩ ማዕድናትና ጌጣጌጥ አቅራቢዎች ጋር ውይይት ተካሄደ
የአዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) ከማዕድን ላኪዎች እና በኢትዮጵያ የከበሩ ማዕድናት እና ጌጣጌጥ አቅራቢዎች እንዲሁም አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ የከበሩ ድንጋዮችን እና ጌጣጌጥ ማዕድናትን ለውጭ ገበያ በብዛት የምታቀርብ ቢሆንም ከዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ግኝት ግን ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲወዳደር አናሳ ነው ተብሏል፡፡
ማዕድናት ላይ እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ አለማቅረብ አንዱ ክፍተት በመሆኑ ሁሉም ላኪዎች እሴት በመጨመር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
ማዕድን ላኪዎቹ በበኩላቸው በዘርፉ አሉ የሚሏቸውን ችግሮች እንዳነሱ ከማእድን ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘርፉ በህግና ስርዓት እንዲመራ ለማድረግ ጠንካራ ማህበር ሊኖር እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡