ስለማር ማወቅ ያለብዎ ነገሮች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማር በንጥረ-ምግቦች እና አንቲኦክሲዳንትስ የበለፀገ ሲሆን ፥ ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪይ አለው፡፡
ማር በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ፥ በቤት ውስጥ ለሚደረግ የህክምና እና የምግብ አማራጭ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡
ማር ፕሮቲን፣ ፋይበር እንዲሁም በውስጡ አነስተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮችን የያዘ በመሆኑ ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው፡፡
የደም ስኳር በተመለከተ ማር ከመደበኛው ስኳር በተሻለ ጥቅም እንደሚሰጥ ይነገራል።
ምንም እንኳን ማር ልክ እንደሌሎች የስኳር ዓይነቶች በደምዎ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ከፍ የሚያደርግ ቢሆንም በውስጡ የያዘው ፀረ-አንቲኦክሲዳንትስ ከሜታቦሊክ ሲንድረም እና ከዓይነት 2 የስኳር በሽታ ቢከላከልም በመጠኑ መወሰድ እንደሚገባው ይመከራል።
ተመራማሪዎች ማር እብጠትን የሚቀንስ እና የደም ስኳር ቁጥጥርን የሚያሻሽል የአዲፖኔክቲን መጠንን እንደሚጨምር ደርሰንበታል ብለዋል።
ማር የልብ ጤንነትን ይጠበቃል፤ አንድ ጽሁፍ እንደሚለው ማር የደም ግፊትን ለመቀነስ፣ በደም ውስጥ የሚገኝን የቅባት መጠን ለማሻሻል፣ የልብ ምትን ለማስተካከል እና ጤናማ ሴሎች እንዳይሞቱ እንደሚረዳም ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም የኮሌስትሮል መጠንን ለማስተካከል እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡
ማር ፀረ-ባክቴሪያ በመሆኑ የቃጠሎ አደጋን እና ቁስልን እንዲሁም የቆዳ ላይ ችግሮች ለማከም ፍቱን እንደሆነ ይነገራል፡፡
ከአንድ ዓመት በላይ ለሆኑ ህጻናት ማር እንደ ተፈጥሯዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሳል መከላከያ እንደሆነ የሚመከር ሲሆን ፥ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከተወሰኑ የሳል መድሃኒቶች የበለጠ ውጤታማ እንደሆነም ያነሳሉ፡፡
እንዲሁም ከ 1 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ማር መብላት እንደሌለባቸው የኽልዝላይን መረጃ ያስጠነቅቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የጤና ችግር ካለብዎ ማር ከመውሰድዎ በፊት ከሃኪምዎ ጋር በመነጋገር ለጤናዎ የሚያመጣው ተጽዕኖ እንደሌለ እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ ቢሆን የተሻለ እንደሆነም ይመከራል፡፡