Fana: At a Speed of Life!

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ለስደት ተመላሾች ማቋቋሚያ የሚውል የ1 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ለስደት ተመላሾች ማቋቋሚያ የሚውል የ1 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ድጋፉ ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱ 18 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመቀበል እና በመጠለያ ለሚያርፉ ተመላሾች ሰብዓዊ ድጋፎችን ለመስጠት እንዲሁም ህገ-ወጥ የሰዎችን ዝውውር ለመከላከል የሚያስችሉ የህብረተሰብ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚውል ነው ተብሏል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደር ፉሃድ ኦባይዱላህ በበኩላቸው÷ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ለወደፊትም ድጋፍ  ማድረጉን እንደሚ ሚቀጥልና ከስደት ተመላሾችን ለመቋቋም በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን  እንዲሁም በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በትብበር ይተገበራል ተብሏል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ ፕሮጀክቱ የንጉስ ሳልማን የሰብአዊ ድጋፍና እርዳታ ማዕከል በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኩል ተደራሽ የሚሆንና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ነው መባሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.