Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካና ቻይና ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ቻይና ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል መስማማታቸው ተነገረ፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሳን ፍራንሲስኮ የባህር ወሽመጥ አካባቢ ከቻይና ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ይህም በዓመታት ውስጥ “በጣም ውጤታማ” ከሚባሉት ውይይቶች ውስጥ አንዱ ነውም ተብሏል፡፡

ይህን ተከትሎ ባይደን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዋሽንግተን እና ቤጂንግ ወታደራዊ ግንኙነታቸው ወደነበረበት ይመለሳል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ወደ ግልጽ እና ቀጥተኛ ግንኙነቶች ተመልሰናል” ያሉት ባይደን፥ ይህም በሁለቱ ኑክሌር የታጠቁ መንግስታት ጠንካራ ግንኙነት መካከል አደጋዎችን እና አለመግባባቶችን ለማስወገድ ይረዳል ነው ያሉት።

ሆኖም አሁንም ድረስ በአንዳንድ ነገሮች አለመግባባቶች እንዳሉም ባይደን በውይይታቸው ወቅት አምነዋል።

በቻይና የሚተዳደረው ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው፥ የሀገራቱ ግንኙነት በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረቱ በመከላከያ ክፍሎች መካከል የሚደረጉ የስራ ስብሰባዎችንና የሁለትዮሽ የባህር ደኅንነት የምክክር ዘዴን ያካተተ ነው ተብሏል።

“ቻይና አሜሪካ ላይ አታሴርም በተመሳሳይም አሜሪካ ቻይናን ለመጨፍለቅ ማቀድ የለባትም” ሲሉም ሺ ጂንፒንግ ለባይደን ጠጠር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜዎች እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ መቆየታቸውን ጠቅሶ የዘገበው አርቲ ነው፡፡

#China #US

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.