Fana: At a Speed of Life!

የኢንቨስትመንት አስፈጻሚ አካላት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የኢንቨስትመንት አስፈፃሚ አካላት ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በፎረሙ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሚን ጨምሮ የፌዴራል፣የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች የኢንቨስትመንት ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፎረሙን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ኢንቨስትመንት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ በማቀድ፣ በተናበበ እና በተቀናጀ መንገድ በመፈፀም፣ ፍሰቱን በመጨመር ለኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለስራ ዕድል ፈጠራ የላቀ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ማድረግ ስለሚያስችል ቅድሚያ ተሰጥቶታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ልትጓዝ የምትችለው ባለሀብቶች ኢንቨስት ሲያደርጉ እና ወጣቶች ወደ ሥራ ሲገቡ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዖ ማበርከት ይኖርበታል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፎረሙ በዛሬ ውሎው የሁሉንም የፌዴራል፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የሩብ ዓመት አፈፃፅም ሪፖርት ገምግሞ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.