ስፓርት

ኢትዮጵያ ማሊን በደርሶ መልስ 6 ለ 0 አሸነፈች

By ዮሐንስ ደርበው

November 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የማሊ አቻውን በደርሶ መልስ ጨዋታ 6 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 3ኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂዷል፡፡

9 ሠዓት ላይ በተከናወነው የመልስ ጨዋታም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የማሊ አቻውን 4 ለ 0 ረትቷል፡፡

ጎሎቹንም÷ እሙሽ ዳንኤል (ሁለት) በመጀመሪያው አጋማሽ እንዲሁም መዓድን ሣኅሉ እና መሣይ ተመስገን በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአጠቃላይ ውጤት ማሊን 6 ለ 0 ማሸነፉን ተከትሎም ወደ መጨረሻው ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡

በመጨረሻው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዙርም ኢትዮጵያ ከሞሮኮ ጋር የምትጫወት ይሆናል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!