Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ካቢኔ የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የአሥተዳደሩ አስፈፃሚ አካል በ2015 ዓመታዊ የሥራ ግምገማ ወቅት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ሪፎርም መደረግ ያለባቸውን ተቋማት እና አደረጃጀቶች ለይቶ የማሻሻያ ጥናት እንዲደረግ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

በዚህም መሠረት ፦

1ኛ. በማዕከል ደረጃ የሚታየውን የሠራተኛ ክምችት ቁጥር ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ እና ለሕብረተሰቡ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የማይመጣጠን በመሆኑ ሠራተኛውን ከፍተኛ የሥራ ጫና ወዳለባቸው ወረዳ እና ተቋማት ሥርጭት እንዲደረግ እና ይህንንም ተቋማት ሙያዊ እና ተፈላጊ ችሎታን ታሳቢ አድርገው እንዲያስተገብሩ እንዲደረግ፣

2ኛ. በመንግሥት ከሚሠራው ለ3ኛ ወገን ወጪ “አውት ሶርስ” ተደርገው ቢሠሩ ጥሩ እና ተፈላጊውን ውጤት ያመጣሉ ተብለው በጥናት በተለዩት አገልግሎቶች በ3ኛ ወገን እንዲሠሩ እና ሂደቱን በተመለከተ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲሁም የአሥተዳደር ችግር እንዳያጋጥም የሽግግር ሂደት እቅድ ተዘጋጅቶ በጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባር እንዲመራ፤

እንዲሁም በተቋቋመው የሙያተኞች ኮሚቴ ጥናት ተደርጎባቸው ተመልሰው ሪፎርም እንዲደረጉ እና በአዲስ መልክ እንዲደራጁ የተደረጉ ተቋማት ጥናት፣ የአሠራር ሂደት እና አደረጃጀት ሁኔታ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የቀረቡትን የማሻሻያ ሐሳቦች በማየት እና በመመርመር ለምክር ቤት እንዲቀርብ ካቢኔው ውሳኔ ማሳለፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.