ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ባሕር ዳር ከተማ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።
ርዕሰ መሥተዳድሩ ባሕር ዳር ሲደርሱ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር መለሰ ዓለሙን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በተመሳሳይ÷ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ የሚገኘውን 3ኛ ዙር የመንግሥት አመራሮች ዐቅም ግንባታ ሥልጠና ማጠቃለያ ለመስጠት አርባ ምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ከተማ ሲደርሱም÷ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የጋሞ ዞን እና የአርባ ምንጭ ከተማ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።