ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷”ውድ ወንድሜን ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ከኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን በማግኘቴ ደስታ ተሰምቶኛል”ብለዋል፡፡
የተጠናከረው ግንኙነታችን ብሎም ዘርፈ ብዙው ትብብራችን በመተማመን እና ዘላቂነት ላለው ልማት ባለን የጋራ ፍላጎት መሰረት ላይ የፀና ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡