Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የ’ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ’ ጉባዔን ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጀርመን በተከሄደው ‘ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ’ ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በ2017 የጀርመን የቡድን 20 ፕሬዚዳንትነት ዘመን የተጀመረው የቡድን 20 ‘ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ’ ለውጥ ተኮር በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት፣ በቡድን 20 አጋሮች ብሎም ከእነዚህ ባሻገር ባሉ አካላት መካከል የንግግር እና የትብብር መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢኮኖሚ ትብብር እና የግሉን ዘርፍ በማጠናከር በሚመለከተው ክፍለ ውይይት ላይ መሳተፋቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.