ኢትዮጵያ በፓን አፍሪካ ፓርላማ ኮሚቴዎች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ የተመራ ልዑክ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው የፓን አፍሪካ ፓርላማ ኮሚቴዎች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው።
ስብሰባው ሶስት የአፍሪካ ኅብረት ሀገራት በሆኑት ደቡብ አፍሪካ ፣ኢትዮጵያና ቡሩንዲ ተወካዮች መካከል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በውይይቱ የትራንስፖርት፣ የኢንዱስትሪ፣ የኮሙኒኬሽን፣ የኢነርጂ፣ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚቴ አባላት እየተሳተፉ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም የትብብር፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የግጭት አፈታት ኮሚቴ፣ የትምህርት፣ የባህል፣ የቱሪዝም እንዲሁም የሰው ሃብት ኮሚቴ አባላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡