በመዲናዋ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አዲሱ ቡልቡላ መንገድ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
አደጋውን ትናንት ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:19 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አዲሱ ቡልቡላ መንገድ (ጃፋር መስኪድ) ፊት ለፊት ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ያደረሰ ሲሆን÷ እድሜያቸዉ 30 ዓመት የተገመተ ሁለት ወንዶች ህይወታቸዉ አልፏል።
በአደጋዉ ህይወታቸዉን ያጡት ወጣቶች በአካባቢዉ በጥበቃ ስራ ላይ የነበሩ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአደጋዉን ምክንያት በፖሊስ እየተጣራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡