Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከተሞች ልማት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበለጸጉ እና ምቹ ከተሞችን መፍጠር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በቡታጅራ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
 
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱን ጨምሮ የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።
 
መድረኩ በየሴክተሩ የሚስተዋሉ መሰረታዊ ችግሮችን በመለየት እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መግባባት ላይ በመድረስ አጋዥ አቅም መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል፡፡
 
በዚህም ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት የተገልጋይን እርካታ ማሳደግ ዋነኛ ዓላማ መሆኑም ተነግሯል።
 
በ2016 በጀት ዓመት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን የሥራ አቅጣጫዎች ላይ በጥልቀት ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
 
ከአዲሱ ክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘም ሰባት ከተሞች የቢሮ መቀመጫዎች ሆነው መታቀፋቸው የከተሜነት ምጣኔን ከማሳደግ ባለፈ የከተማ እና የገጠር አካባቢዎችን ትስስር እንደሚያጠናክርም ተጠቁሟል።
 
በለይኩን ዓለም
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.