አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በኮምቦልቻ ከተማ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በኮምቦልቻ ከተማ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀምረዋል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የሚገነቡት ቤቶች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚጠይቁ የተገለጸ ሲሆን፤ 50 በመቶው በከተማው በጀት ቀሪው በህብረተሰቡ ተሳትፎ እንደሚሸፈን ተገልጿል።
ግንባታውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን÷ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከ500 በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ በከተማዋ የተሰሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን እንደጎበኙ ከኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡