Fana: At a Speed of Life!

አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎበኙ።

አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ ከከልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ነው በአሶሳ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን የጎበኙት።

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ በከተማው በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ እየተከናወኑ የሚገኙ የወተት፣ የዶሮ እርባታና የእንቁላል ምርት ሥራዎችን ተመልክተዋል።

አቶ ተስፋዬ በልጅጌ÷ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ያሏትን ዕምቅ ሀብቶች ለማልማት እየተደረጉ በሚገኙ ጥረቶች የሚታየው ውጤት፣ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጪ ለማቅረብ የሚያስችል አቅም እንዳለ ማሣያዎች ናቸው ብለዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሠላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን መግለፃቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.