Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዕድገትን በሚያፋጥኑ የልማት ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል – አቶ ጥላሁን

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበረሰብ ዕድገትን በሚያፋጥኑ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

ክልሉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የህዝቦች አብሮነትና መፈቃቀድን መሰረት አድርጎ መመስረቱን ገልጸው፤ የክልሉን ተቋማት በ6 የብዝሃ ማዕከላት በማደራጀት ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰዋል።

በየደረጃው ባለው መዋቅር የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን በመፈተሽ ህዝብን የሚያማርሩ ጉዳዮችን ለመቅረፍ እንደሚሰራ አመልክተው፤ ለዚህም የክልሉ ህዝብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የማህበረሰብ ዕድገትን በሚያፋጥኑ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም አስረድተዋል።

ለክልሉ ሁለንተናዊ ልማት የመንግስትና የህዝብ ተሳትፎን ማጠናከር እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጻቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለከተው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምስረታ መርሃግብር ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም የክልሉ የፖለቲካና የአስተዳደር ማዕከል በሆነችው ሶዶ ከተማ እንደሚያካሂድም ነው የገለፁት።

መርሃግብሩ ለክልሉ ምስረታ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና የሚሰጥበት እንደሆነ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከተለያዩ ተቋማት እና የመንግስት መዋቅሮች የአጋርነት ድጋፍ የምናገኝበት ነው ብለዋል።

በክልሉ ይፋዊ ምስረታ እና ስራ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የ11 ዱም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባዎችን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የፌደራል የስራ ኃላፊዎች አጋር አካላትንና ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.