ተመድና ብሪክስ በእስራዔል-ሃማስ ጦርነት ላይ ሊወያዩ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) እና የብሪክስ አባል ሀገራት በእስራዔል-ሃማስ ጦርነት ላይ ሊወያዩ መሆኑ ተገለጸ።
በውይይቱ የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን እና የቻይናው አቻቸውን ሺ ጂንፒንግ ጨምሮ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ይካፈላሉ ተብሏል፡፡
በበይነ-መረብ በሚካሄደው በዚህ ውይይት የብሪክስ አባላቱ መሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በመጪው ጥር በይፋ ብሪክስን ይቀላቀላሉ የተባሉት ሀገሮች እንደሚሳተፉ ተነግሯል።
የውይይት መድረኩን የወቅቱ የብሪክስ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንደሚመሩት የተጠቆመ ሲሆን በጋዛ ባለው ሰብዓዊ ቀውስ ላይ ተነጋግረው የጋራ መግለጫ እንደሚያወጡ ተነግሯል።