ሚኒስቴሩ ከ21 ኩባንያዎች ጋር ለመሥራት በሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ መከረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ከፈረንሳይ የግል ኩባንያዎች ማኅበር ከተወከሉ 21 ኩባንያዎች ከተውጣጡ 30 የልዑካን ቡድን ዓባላት ጋር ተወያየ፡፡
በውይይቱም÷ የኢትዮጵያና ፈረንሳይን ግንኙነት በኢንቨስትመንት ዘርፉ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ልዑኩ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) አድንቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ዕምቅ ዐቅም እንዳላትም አብራርተዋል፡፡
የፈረንሳይ ኩባንያዎች መዋዕለ-ንዋያቸውን በመሠረተ-ልማት ዘርፉ በማዋል የሁለቱን ሀገራት የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግና የልማት አጋርነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡
ኩባንያዎቹ በየትኞቹ የልማት ዘርፎች ላይ ቢሰማሩ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገለጻ መደረጉንም የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
መንግሥት የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማሳደግ የነደፋቸው ስትራቴጂዎችም ተብራርተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ዓባላትም ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለጻ አመስግነው÷ ኢትዮጵያ በዕድገት ጎዳና ላይ እየተራመደች መሆኗን አድንቀዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!