Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ ከኮሪያ ልዑክ ጋር በሚሠራባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከኮሪያ ልዑካን ቡድን ጋር በቀጣይ በሚሠሩባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በሊ ሔኢሲኦክ የተመራ የኮሪያ የልዑካን ቡድን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ዴዔታ ምኅረቱ ሻንቆ (ረ/ፕ) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም እንደ ሀገር የሚያጋጥሙ ችግሮችን በብቃት ለመወጣት እንዲቻል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ዐቅም ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላት ኮሪያ አሁን ለደረሰችበት የሥልጣኔ ደረጃ ለመድረስ ያለፈችባቸውን የልማትና የዕድገት ጉዞ የልምድ ልውውጥ ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.