Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቡሶች ወደ ስራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባን የብዙሃን ትራንስፖርት አቅርቦት ለማሻሻል ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቡሶች ዛሬ ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ የአዲስ አበባን የብዙሃን ትራንስፖርት አቅርቦት ለማሻሻል ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቡሶችን ወደ ስራ አስገብተናል ብለዋል፡፡

ዛሬ ወደ ስምሪት ያስገባናቸውን ጨምሮ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ 177፣ በከተማው በጀት 200 በጠቅላላ 377 አዳዲስና ዘመናዊ የከተማ አውቶቡሶችን ገዝተን ወደ ስራ አስገብተናል ነው ያሉት፡፡

ዓለም ባንክ ላደረገልን ድጋፍም እናመሰግናለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አውቶብሶቹ በመዲናዋ ከፍተኛ የትራንስፖርት ተጠቃሚ በሚበዛባቸው መስመሮች ላይ እንደሚመደቡ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.