Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ የ15 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በሉሰፈር እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ የ15 ዓመት ታዳጊ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊውን አስከሬን አውጥተው ለፖሊስ እንዳስረከቡም ተገልጿል፡፡

ታዳጊው ህይወቱ ያለፈበት ጉድጓድ ታዳጊዎችና ወጣቶች ዋና ለመዋኘት እየገቡ በተደጋጋሚ ህይወታቸውን የሚያጡበት ነው ተብሏል፡፡

ከሶስት ቀናት በፊት ሕዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም በዚሁ ክፍለ ከተማ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ውሃ ባቆረ ጉዳጓድ ውስጥ ዋና ለመዋኘት የገባ የ19 ዓመት ወጣት ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡

በአዲስ አበባ በተለያየ አካባቢ ተቆፍረው ክፍት የተተዉና ውሃ ያቆሩ ጉድጓዶች መፍትሄ ባለማግኘታቸው አሁንም ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት እየሆኑ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ጠቁሟል፡፡

የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ መፍትሄ እንዲሰጡም ማሳሰቡን ከኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.