በአፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ ጂግጂጋ ገባ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጂግጂጋ ከተማ ገብቷል፡፡
ልዑኩ ወደ ጂግጂጋ ያቀናው የ18ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ቅድመ ዝግጅት ለመመልከት መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ ገልጸዋል፡፡
የሶማሌ ክልል 18ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስመልክቶ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን፣ የብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን አንድነት የሚያጠናክሩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
በአፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የተመራው ልዑክም ወደ ክልሉ የሄደው እነዚህን ተግባራት ለመመልከት ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት እንግዶችን ለመቀበልና በዓሉን በድምቀት ለማክበር እያደረገ ያለው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ከተገመገመ በኋላ በቀሪ ሥራዎች ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም አመላክተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!