ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በማዕድን ዘርፍ ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በማዕድን፣ ታዳሽ ኃይል፣ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ትብብር ማድረግ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ገለጹ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ልዩ ተወካይ ፒተር ላውንስኪ-ቲፈንታል ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በኢኮኖሚያዊ እድሎች እና የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ቀጣናዊ ልማቶች ላይ ትኩረት ማድረጉ ተገልጿል።
አምባሳደር ምስጋኑ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኦስትሪያ ኤምባሲ የሁለቱን ሀገራት ተምሳሌታዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስቀጠል አበረታች ሚና ይጫወታል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ልዩ ተወካይ ፒተር ፥ ኦስትሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የረጅም ጊዜ ወዳጅነት እንዳላት ገልፀው እንደ ማዕድን፣ ታዳሽ ሃይል፣ ግብርና እና የእንስሳት እርባታ ባሉ ዘርፎች ለመተባበር ፍላጎት እንደላት ተናግረዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!