ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ 16 ሺህ ቶን ሩዝ በእርዳታ ለገሰች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ደቡብ ኮሪያ በድንበር ተሻጋሪ የምግብ ድጋፍ ፕሮግራሟ አማካኝነት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአራት የመካከለኛው ምስራቅና የአፍሪካ አገራት 50 ሺህ ቶን የሩዝ ምርት ድጋፍ ማድረጓን የአገሪቱ የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
አገሪቱ በዓለም የምግብ ድርጅት አማካኝነት 19 ሺህ ቶን ሩዝ ለየመን፣16 ሺህ ቶን ለኢትዮጵያ፣10 ሺህ ቶን ለኬንያ፣ 5 ሺህ ቶን ደግሞ ለኡጋንዳ ድጋፍ አድርጋለች።
ደቡብ ኮሪያ በፈረንጆቹ በ2018 እና 2019 ለአገራቱ 100 ሺህ ቶን የሩዝ ምርት ድጋፍ ያደረገች ሲሆን የአሁኑ እገዛ ለሶስተኛ ጊዜ የተደረገ መሆኑም ተገልጿል።
እርዳታውን የጫኑት መርከቦች ባለፈው ሳምንት ከአገሪቱ መንቀሳቀሳቸውም በመረጃው ተጠቅሷል።
የተላከው የሩዝ ምርት በአጠቃላይ በአውሮፓዊያኑ 2018 የምርት ዘመን የተሰበሰበ ሲሆን የማጓጓዝና የማከፋፈል ሃላፊነቱ በመንግስታቱ ድርጅት የምግብ ድርጅት ስር ነው ተብሏል።
የእርዳታው ዋነኛ ግብ ዓለም አቀፍ የምግብ ዋስናን ለማረጋገጥና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወደ ኋላ የቀሩ አገራት ለመደገፍ መሆኑን ዮናፕ የተሰኘውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።