ስፓርት

ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

By ዮሐንስ ደርበው

December 06, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በውሃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች፡፡

የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርት ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 8ኛው የዞን 3 አፍሪካ ውሃ ዋና ሻምፒዮና በማስተርስ ዋና ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በዞን 3 የአፍሪካ ውሃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር በታዳጊ ወጣቶችና በማስተርስ ዋና ውድድር ተሳትፋ በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ እና በ100 ሜትር ደረት ቀዘፋ በአትሌት እስከዳር አቻምየለህ አማካኝነት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ ማስመዝገቧን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡