ስፓርት

የአትሌት ድርቤ ወልተጂ የ1 ማይል ርቀት ክብረወሰን ፀደቀ

By Feven Bishaw

December 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ድርቤ ወልተጂ የአንድ ማይል ርቀት ክብረወሰን በአለምአቀፉ  አትሌቲክስ እውቅና አግኝቷል።

 

ለመጀመሪያ ጊዜ በላቲቪያ ሪጋ በ1 ማይል ርቀት በተካሄደው የሴቶች ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ4 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ከ98 ማይክሮ ሰከንድ  በመግባት የርቀቱን ክብረወሰን ማሻሻሏ የሚታወስ ነው።