ቢዝነስ

በኢትዮጵያ ባሉ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ከኳታር ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

December 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ከኳታር ባለሃብቶች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያን ወጪ ምርቶች በመቀበል እና በሀገራችን መዋዕለ-ነዋያቸውን ኢንቨስት በማድረግ ረገድ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ስጋቶችን እንዲሁም ስላለው ምቹ ሁኔታ ከባለሃብቶቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ስለሚኖረው ትብብር እና የንግድ ልውውጥ ዙሪያ ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውንም አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!