ስፓርት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀናው

By ዮሐንስ ደርበው

December 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሳስ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 4 ለ1 አሸንፏል፡፡

የሲዳማ ቡናን ጎሎችም÷ በዛብህ መለዮ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ፣ ማይክል ኪፕሮል እና ቡልቻ ሹራ አስቆጥረዋል፡፡

የወላይታ ድቻን ብቸኛ ጎል ደግሞ ዮናታን ኤልያስ በሁለተኛው አጋማሽ ማስቆጠር ችሏል፡፡

ሲዳማ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስምንት በማድረስ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ወላይታ ድቻ በ11 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!