ስፓርት

ለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ማጠናቀቂያ ከ900 ሚሊየን ብር በላይ ተፈቀደ

By Feven Bishaw

December 19, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ የቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ከ900 ሚሊየን ብር በላይ መፈቀዱን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ምስክር ሰውነት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷የማጠናቀቂያ ስራ ስታዲየሙ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ወደ ማስተናጋድ እንዲመለስ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

የሁለተኛው ዙር ግንባታ በተያዘው የበጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቅ እቅድ መያዙም ተመላክቷል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም መመዘኛ መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን እንዳያስተናግድ ማገዱ ይታወሳል። በወርቅነህ ጋሻው