የሀገር ውስጥ ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ከኩዌት አቻቸው ጋር  በስልክ ተወያዩ

By Meseret Demissu

May 28, 2020

አዲስ አበባ፣ግንቦት 20፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ ከኩዌት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኻሊድ አል ጃረላህ ጋር በስልክ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ደህንነት በሚጠበቅበትና በፍላጎታቸው ወደአገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች እየተደረገ ስላለው ቅድመ ዝግጅት  መረጃ  ተለዋውጠዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ የሥራ ኃላፊዎች በሁለትዮሽ፣ በክልላዊና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዳዮች በትብብር መስራት በሚቻልባቸው  መንገዶች ላይ  መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።