የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 100 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

By Tibebu Kebede

May 28, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 950 የላብራቶሪ ምርመራ 100 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 831 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው እለት ባወጡት ሪፖርት ገልፀዋል።