ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፑሽኪን አደባባይ ጎተራ ድረስ እየተገነባ ያለውን የመንገድ ግንባታ ሂደት ተመለከቱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ኢንጂነር ታከለ ኡማ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ከፑሽኪን አደባባይ ጎተራ ድረስ እየተገነባ ያለውን የመንገድ ግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።
በአሁኑ ወቅት የመንገዱ 320 ሜትር የሚሸፍን የዋሻ ቁፋሮው እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከፑሽኪን አደባባይ ጎተራ ድረስ እየተገነባ ያለው መንገድ 320 ሜትር ርዝመት ካለው ዋሻ በተጨማሪ የፈጣን አውቶብስ መተላለፊያ ይኖረዋል ነው የተባለው።
ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ዘጠኝ ወራት ያስቆጠረ ሲሆን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ከፑሽኪን አደባባይ ጎተራ የሚገነባው መንገድ ሲጠናቀቅ የመንገድ አማራጭ ከመፍጠሩ ባለፈ በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ያቃልላል ነው የተባለው።
ከዚያም ባለፈ መንገዱ የከተማዋን ውበት በመጨመር በኩል አስተዋፅኦው የጎላ ነው መባሉን ከከንቲባ ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።