ስፓርት

ቪክቶር ኦሲሜን በናፖሊ ኮንትራቱን አራዘመ

By Mikias Ayele

December 23, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጀሪያዊው አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን በናፖሊ እስከ 2026 የሚያቆየውን ተጨማሪ ኮንትራት ውል ፈርሟል፡፡

በአዲሱ ኮንትራት ሥምምነት የወጣቱ አጥቂ ፈላጊ የሆነ ክለብ 130 ሚሊየን ዩሮ መክፈል ይጠበቅበታል።

ኦስሜን በ2022 የስኮዲቶ ሻምፒዮን ከሆነው ናፖሊ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን 26 ጎሎችን በማስቆጠር የሴሪ አው ኮከብ ገል አግቢ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡

የ24 ዓመቱ አጥቂ በጥር የዝውውር መስኮት ቼልሲን ጨምሮ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቢቆይም በኔፕልሱ ክለብ ለተጨማሪ ዓመታት እንደሚቆይ ተረጋግጧል፡፡