ቢዝነስ

ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ የሻይ ቅጠል ተክል ልማት እንዲስፋፋ በትኩረት ይሠራል አሉ

By ዮሐንስ ደርበው

December 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል እየተሠራ ያለው የሻይ ቅጠል ተክል ልማት እንዲያድግ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አስታወቁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በጎደሬ ወረዳ ጉማሬ ቀበሌ የሕንድ ቨርዳንታ ኢንቨስትመንት ኩባንያ የሻይ ተክል ልማትና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የሻይ ቅጠል ልማት ለሀገር ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ይረዳል ብለዋል፡፡

በመሆኑም እየተሠራ ያለው ልማት እንዲያድግ የክልሉ መንግሥት ሚና ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ከ360 ሄክታር በላይ የሻይ ቅጠል ተክል ማልማቱ እና ፋብሪካ በማቋቋም ምርቱን ለገበያ እያቀረበ መሆኑም ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!