ስፓርት

በአዲስ አበባ ደርቢ ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን አሸነፉ

By Mikias Ayele

December 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥብ አሳክቷል፡፡

9፡00 ላይ በተደረገው ተስተካካይ ጨዋታ የቡናማዎቹን ብቸኛ ጎል ጫላ ተሺታ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ለመጋራት በተደጋጋሚ ያደረገውን ሙከራ ወደ ውጤት መቀየር ሳይችል ቀርቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና በ11 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ፈረሰኞቹ በ16 ነጥቦች በነበሩበት 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡