ቢዝነስ

ሕንድ ለገቢ ንግድ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሯ የመገበያያ ገንዘብ ክፍያ ፈጸመች

By Alemayehu Geremew

December 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕንድ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ለገዛችው ድፍድፍ ነዳጅ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሯ የመገበያያ ገንዘብ ሩፒ ክፍያ መፈጸሟ ተሰምቷል፡፡

የዓለማችን ሦስተኛዋ የኃይል ተጠቃሚ ሀገር የገቢ ንግድ ክፍያዋን በሩፒ መፈጸሟ ገንዘቧን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እንደሚያስችላት ተገልጿል፡፡

ሕንድ አሁን እያስተዋወቀች ያለችው ሥልት የነዳጅ አቅራቢዎችን ለማብዛት እና የውጭ ምንዛሬ ወጪዋን ለመቀነስ የያዘችው ሰፊ ዕቅድ አካል መሆኑን ቢዝነስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

ይህ የግብይት ሥርዓትም ቀደም ሲል የሕንድ ቁጠባ ባንክ አስመጪ እና ላኪዎች ክፍያቸውን በሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ እንዲፈፅሙ ከሚፈቅደው ውሳኔ ጋር የሚሄድ መሆኑም ነው የተመላከተው፡፡