ስፓርት

ኡጋንዳዊው አትሌት በኬንያ መኪና ውስጥ ሕይወቱ አልፎ ተገኘ

By Melaku Gedif

January 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡጋንዳዊው አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት በኬንያ መኪና ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተሰምቷል፡፡

በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች በ3 ሺህ መሰናክል ሀገሩን የወከለው አትሌት ኪፕላጋት አንገቱና ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ሕይወቱ ማለፉን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የ34 ዓመቱ ኪፕላጋት ታዋቂ አትሌቶች ልምምድ በሚያደርጉባት ኤልዶሬት በተሰኘችው የኬንያ ከተማ ውስጥ ነው ሕይወቱ አልፎ የተገኘው፡፡

የኬንያ ፖሊስ የአትሌት ኪፕላጋት አሟሟት ሁኔታ ላይ ምርመራ ማድረግ እንደጀመረ ማስታወቁንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡