የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

May 29, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታዎችን በማስተባበር ስለምትጫወተው ሚና፣ በዚህ ዓመት የአረንጓዴ ሻራ ዕቅዶች ድጋፍ ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ የምግብ ደኅንነትን ለማረጋገጥና ምርታማነትን ለማሳደግ ስለምታደርገው ጥረትም መክረዋል።