Fana: At a Speed of Life!

በዱከም ከተማ በ400 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ዱከም ከተማ በ400 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

በዛሬው እለት የተመረቁት ፕሮጀክቶች 48 ሲሆኑ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በተገኙበት መመረቁን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

ከመሰረተ ልማቶቹ ውስጥ የአረንጓዴ እና የመዝናኛ ቦታዎች ይገኙበታል ተብሏል።

መሰረተ ልማቶቹ በመንግስት ድጋፍ እና በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ መሆናቸውም በምርቃት ስነ ስርአቱ ወቅት ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.