ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን ረቱ

By Tamrat Bishaw

January 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

9፡00 ላይ ኢትዮጵያ መድንን የገጠመው ሲዳማ ቡና በይገዙ ቦጋለ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 11 ከፍ በማድረግ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ኢትዮጵያ መድን ደግሞ በነበረበት 8ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር 12፡00 ላይ አዳማ ከተማን የገጠመው ሀድያ ሆሳዕና በሰመረ ሀፍተይ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ነብሮቹ ነጥባቸውን ወደ 11 ከፍ በማድረግ ከኢትጵያ ቡና፣ ወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ጋር እኩል 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

እንዲሁም አዳማ ከተማ በ13 ነጥቦች በነበረበት 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡