የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የተሃድሶ ሠልጣኞች የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተሃድሶ ሥልጠና ሲወስዱ የነበሩ 852 ግለሰቦች የተሳተፉበት የማጠቃለያ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ እየተካሔደ ነው።
በመድረኩ የጎንደር ቀጣና ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ጀኔራል ዋኘው አለሜ፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ ወርቁ ኃይለማሪያም እና ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ስልጠናቸውን አጠናቅቀው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉት ሰልጣኞች ለአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላምና ልማት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ግንዛቤ ተጠቅመው ለአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል፡፡
በቆይታቸው ከፈጸሙት ሥህተት ተምረው ለዘላቂ ሰላም መስፈን የበኩላቸው ለመወጣት ዝግጁ እንደሆኑም አረጋግጠዋል፡፡
የተፈጠረላቸው ግንዛቤ በመጠቀም የተሳሳቱትን ወደ ሰላም እንዲመጡ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ መጥቀሳቸውንም የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡