Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለዓይነ ስውራን የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ለዓይነ ስውራን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ጽህፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ÷ በየዓመቱ ታኅሣስ 26 ቀን የሚከበረው የዓለም የብሬል ቀን ለዓይነ ስውራን ተደራሽነትን እንደሚያስታውስ አመልክቷል፡፡

የብሬል ፈጣሪ የሆነው ሉዊስ ብሬል በዚህ ቀን እንደሚታወስም ነው የገለጸው፡፡

ጽህፈት ቤቱ ፥ ዓይነ ስውራን በየቀኑ ብዙ ፈተናዎች የሚያጋጥሟቸው በመሆኑ በሁሉም አቅጣጫ መደገፍ እና ተካታችነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብሏል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ለብሬል ተጠቃሚዎችም ለዓለም የብሬል ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ለዓይነ ስውራን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጡንም የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.