Fana: At a Speed of Life!

የዱብቲ ሆስፒታል እድሳትና የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዱብቲ ሆስፒታል እድሳት እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የዱብቲ ሆስፒታል ካለፉት 50 ዓመታት በላይ ማህበረሰቡን እያገለገለ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንዳሉት፥ በተለይም ባለፉት ዓመታት ድንገተኛ ወረርሽኞች እንዲሁም ግጭቶች ሲያጋጥሙ ምላሽ ሲሰጥና ማህበረሰቡን ሲያገለግል የቆየ ተቋም ነው፡፡

በመሆኑም ሆስፒታሉ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ችግሮች ስላሉት እድሳቱ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የሆስፒታሉ እድሳት የድንገተኛ አደጋ ምላሽን ለማሳደግ ከዓለም ባንክ በተገኘ ፈንድ የሆስፒታሉ እድሳት ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲሰራ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡

በቀጣይም በግጭት የተጎዱ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ጤና ተቋማት እድሳት ፕሮጀክት ውስጥ በአፋር ክልል በግጭቱ የተጎዱ 20 ጤና ጣቢያዎች እድሳት እንደሚደረግ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በሆስፒታሉ የሚታዩ የመሰረተ ልማትና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት የዓለም የጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍ፣ በፌት ፋውንዴሽን፣ አኤምአኤስአኤፍ እና ሌሎች አጋር አካላትም ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሃቢብ እንዳሉት፥ ሙሉ እድሳት የሚደረግለት የዱብቲ ሆስፒታል ለሰራተኞቹ እና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ምቹ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም በዱብቲ ሆስፒታል ግንባታው ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የቆየና በአሁኑ ጊዜ ግን ሊጠናቀቅ የተቃረበው የዱብቲ ሪጅናል ላብራቶሪንም ለማጠናቀቅ እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

በዱብቲ ሆስፒታል በቅርቡ በበፌት ፋውንዴሽን ድጋፍ ተገንብቶ እየተጠናቀቀ ያለውን የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል ያለበት ደረጃ መጎብኘቱንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.