Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሮኒክ አማራጭ በመገበያየት እራስን ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕብረተሰቡ በተቻለ መጠን በኤሌክትሮኒክ አማራጮች በመገበያየት በበዓል ሰሞን በስፋት ከሚስተዋሉ መልከ-ብዙ መጭበርበሮች እራሱን እንዲጠብቅ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ፡፡

ከግብይት ጋር በተያያዘ በየትኛውም ጊዜ የመጭበርበር ሥጋት ቢኖርም በበዓል ሰሞን የማጭበርበር ድርጊት በተለያየ መንገድ በብዛት እንደሚስተዋል የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ እንዳለ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አንጻር ሁኔታዎች የሚፈቅዱላቸው እና ዕድሉ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ግብይትን እንዲፈጽሙ፤ ዕድሉን ያላገኙ ካሉም ግብይት ሲፈጽሙ በከፍተኛ ጥንቃቄ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም ሰሞኑን ከሚከበረው የገና (የልደት) በዓል ጋር በተያያዘ÷ በበዓላት ወቅት ሐሰተኛ የሆኑ የብር ኖቶች በአንፃራዊነት በወንጀል ፈፃሚ አካላት በግብይት ላይ የማዋል አዝማሚያ ስለሚጨምር ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ መሠረትም÷ ግብይት ሲፈፀም በተቻለ መጠን በተረጋጋና በጥንቃቄ ማከናወን፣ የብር ኖቶችን ትክክለኛነት ማረጋገጥና መገበያየት ይገባል ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል በራስም ሆነ በሌሎች ሰዎች በሚደረግ ግብይት አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥም ለሕግ አስከባሪ አካላት ማሣወቅ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.