አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶስት ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና ሩሲያ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር፣ በቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ለመለዋወጥ እና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የትብብር ዘርፎችን ለመለየት ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በኢትዮጵያ የብሪታንያ አምባሳደር ዳረን ዌልች በቀጠናው ያለውን እድገት በማድነቅ በሚመለከታቸው አካላት መካከል እየተደረገ ያለውን የሰላም ንግግር አበረታተዋል።
ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም የኢኮኖሚና ንግድ አጋርነት ያላትን ሚናም ጠቅሰዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ ከፈረንሳዩ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ጋር የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን መደገፍ በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።
ከዚህ ባለፈም ሽብርተኝነትን መከላከል በሚቻልበት አግባብ እና በባህል፣ በትምሕርት እና ቱሪዝም ዘርፎች ያለውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር አድርገዋል።
ከሩሲያው አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርክሂን ጋር በነበራቸው ቆይታም፥ ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር የምታደርገውን ጥረት ጨምሮ በሌሎች ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም ትብብርን ማሳደግ እና የጋራ ልምምድ ማድረግ የሚቻልባቸውን እድሎች መለየት ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ አንስተው መክረዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!