በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የዕርድ እንስሣት ዋጋ መረጋጋት አሳይቷል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሞኑ የበዓል ግብይት ላይ የዕርድ እንስሣት ዋጋ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መረጋጋት ማሳየቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በሰሞኑ የበዓል ገበያ የዕርድ ሠንጋ ከ40 ሺህ እስከ 110 ሺህ ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሮት ዳይሬክተር ገምቴሳ ነጋዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በግ እና ፍየል ከ4 ሺህ እስከ 12 ሺህ ብር እየተሸጠ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በተደረገ ምክክርም በቂ የሽንኩርት ምርት ከሱዳን እንዲገባ በመደረጉ አሁን ላይ አንድ ኪሎ ከ140-145 ብር ለግብይት ቀርቧል ነው ያሉት፡፡
ከላይ የተገለጹት ዋጋዎች ከበዓል ሰሞን በፊት ከነበረ ግብይት አንጻር ቅናሽ የታየባቸው መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በኡራ እና አብርሃሞ ወረዳዎች የሚመረቱ የግብርና ምርቶችም ከደላላ ሠንሠለት ነጻ ሆነው በቀጥታ ለሸማቹ እንዲደርሱ እየተደረገ መሆኑን ነው ያነሱት፡፡
በአንጻሩ ክልሉ ከሚዋሰንባቸው ክልሎች ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የጤፍ እና የኢንዱስትሪ ምርቶች እጥረት መስተዋሉን ጠቁመዋል፡፡
ለአብነትም ወደ ክልሉ መግባት የነበረበት 30 ሺህ ኩንታል ስኳር በጸጥታ ችግር ምክንያት እስካሁን አለመድረሱን ተናግረዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!