ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

By Mikias Ayele

January 05, 2024

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል።

ከቀትር በኋላ በተካሄደ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ጎሎች ጌታነህ ከበደ እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ አስቆጥረዋል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የድል ጎሎቹን መስፍን ታፈሰ ሲያስቆጥር አቤኔዘር ዮሐንስ ደግሞ የሐዋሳ ከተማን የማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።