Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዋሬ አካባቢ የተገነባውን የአነስተኛ ወጪ ቤቶች ግንባታ መረቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዋሬ አካባቢ በ1 ሺህ 523 ነጥብ 3 ሜትር ካሬ ላይ የተገነባውን ተጨማሪ የአነስተኛ ወጪ ቤቶች ግንባታ መርቀዋል።

የተመረቁት ሁለቱ ባለ 11 ወለል ህንፃዎች በሶስት ወራት ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ’መደመር ትውልድ መጽሓፍ ሽያጭ ገቢ እና ከኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ድጋፍ የተገነቡ ናቸው።

ህንፃዎቹ ባለአንድ፣ ባለሁለት እና ባለሦስት የመኝታ ክፍሎች ያላቸው 110 ቤቶች እንዲሁም የታችኛው ወለል ላይ 51 የምድር ቤት ክፍሎችን የያዙ ናቸው።

በተጨማሪም የጋራ የእንጀራ እና ዳቦ መጋገሪያ፣ ማብሰያ እና የማጠቢያ አካባቢዎች እንደተካተቱባቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላታል፡፡

ሁለቱ አፓርትመንቶች በጠባብ ቦታ ላይ ለየአገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ የመጠቀም ጥበብ ያረፈባቸው ሲሆኑ÷ ሁሉም ቤቶች ሙሉ እቃ የተሟላላቸው መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ባለሃብቶች በበጎ አድራጎት እና ፈጠራ የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ አርዓያነትን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.