በአዲስ አበባ ከተማ ከ263 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ263 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሀገር ባለውለታዎችና በከተማዋ የሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ይገኙበታል።
የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ የተደረገው ከተለያዩ አካላት በተገኘ ከ750 ሚሊየን ብር በላይ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ÷ ማዕድ ማጋራታችን ሀገራችሁን ስታገለግሉ የነበራችሁ የሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካሞች ከጎናችሁ እንደሆንን እንድታስቡ ነው ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ በመሳተፍ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አብሮነታቸውን ላሳዩ ባለሀብቶችና ተቋማት ምስጋና አቅርበው፤ ሌሎች አካላትም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በታሪኩ ወ/ሰንበት