Fana: At a Speed of Life!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር የእንኳን ለክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ።

አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በመልዕክታቸው÷ በክርስቶስ ልደት በብዝኀነት በእኩልነት መኖርንና ለአንድ ዓላማ መኖርን በአንድነት መሰለፍን እንማርበታለን ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ብዝኀ ማንነት ያለን ሕዝቦች ነን ያሉት አፈ ጉባዔው÷ ልዩነታችንን ወደ ጎን በመተው በእኩልነትና በአንድነት ከቆምን በሀገራችን ሰላምን እናሰፍናለን፤ ብልጽግናችንም እናረጋግጣለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የክርስቶስ ልደት ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን፣ ከኦሪትነት ወደ ሀዲስነት መለወጥን እንደሚያስረዳ ጠቅሰው÷ ለውጥ ከነባር ወደ አዲስና የተሻለ ማንነት መሸጋገር ነው ብለዋል፡፡

ወደሚያልሙትና ተስፋ ወደሚያደርጉት ነገር ለመድረስ ጉዞ መጀመር እንደሚያስፈልግ በመግለጽነው ኢትዮጵያ በለውጥ ጉዞ ላይ ናት ሲሉ ገልጸዋል።

በሰንካላ ምክንያቶች ለውጡ ሳይቀለበስ ከምንመኘውና ከምናልመው ግብ ላይ ለመድረስ፣ ከድህነት ወደ ብልጽግና ለመሸጋገር ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከአሮጌውና ልዩነትን ከሚያቀነቅነው ስሁት ትርክት ወጥተን ወደ አዲስና የጋራ አስተሳሰብ እንድንሸጋገር አደራ እላለሁም ብለዋል፡፡

በክርስቶስ ልደት የቆየ የጥል ግድግዳ ተደርምሶና የልዩነት አጥር ፈራርሶ በአብሮነትና በፍቅር ሁሉም ዘምረዋል ያሉት አቶ አገኘሁ÷ ጥላቻና ያልተገባ ልዩነት መጠፋፋትን እንጂ መደጋገፍን አያመጣም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ልዩነቶችን በማስወገድ የጋራ እሴትንቶ እያጠናከሩ መጪውን ጊዜ ማሳመር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.